ውሳኔ መወሰን
ከሆነ፣ ግን፣ አለበለዚያ — እና የቃላት ቅደም ተከተል
ፕሮግራም ሁልጊዜ ከላይ ወደ ታች ብቻ አይሄድም። አንዳንድ ጊዜ "ይህ እውነት ከሆነ ይህን አድርግ" ማለት ያስፈልጋል።
ትልቅ ሰው
ሁኔታው ቀድሞ ይመጣል
ይህ የአሃዱ ዋና ልዩነት ነው። በእንግሊዝኛ ላይ በተመሠረቱ ቋንቋዎች "if age > 18" ይባላል — ቃሉ ቀድሞ፣ ሁኔታው ኋላ። በአማርኛ ግን እንዲህ አንናገርም። "ዕድሜው ከ18 በላይ ከሆነ" እንላለን — ሁኔታው ቀድሞ፣ ቃሉ ኋላ።
አሃዱ የሚከተለው አማርኛውን ነው፦
ዕድሜ > 18 ከሆነ፦ስለዚህ ኮዱን በድምጽ ሲያነቡት እንደ ዓረፍተ ነገር ይሰማል። ፦ ደግሞ "ይህን
ተከትሎ የሚመጣው…" ማለት ነው።
ሁለት መንገድ
ሁኔታው እውነት ካልሆነ ምን ይሁን? አለበለዚያ ይላል።
ልጅ
ከሁለት በላይ
ግን ተጨማሪ ሁኔታ ይጨምራል። ልብ ይበሉ — ግን ቀድሞ፣ ሁኔታው ከዚያ፣ ከሆነ
ኋላ ይመጣል።
ሲ
ከላይ ወደ ታች ይፈተሻል። የመጀመሪያው እውነት የሆነው ይሄዳል፤ የቀሩት አይታዩም።
የማነጻጸሪያ ምልክቶች
| ምልክት | ትርጉም |
|---|---|
> |
ይበልጣል |
< |
ያንሳል |
>= |
ይበልጣል ወይም እኩል ነው |
<= |
ያንሳል ወይም እኩል ነው |
== |
እኩል ነው |
!= |
እኩል አይደለም |
= እና == የተለያዩ ናቸው። = ዋጋ ያስቀምጣል፤ == ያነጻጽራል።
ሁኔታዎችን ማገናኘት
እና፣ ወይም፣ አይደለም ሁኔታዎችን ያገናኛሉ።
ብድር ይፈቀዳል
ክፍተት ይቆጠራል
ከ፦ በኋላ ያለው መስመር ወደ ውስጥ መግባት አለበት። የገባው ሁሉ የዚያ ሁኔታ አካል ነው።
ጥንድ ነው
ይህም የሁኔታው አካል ነው
ይህ ግን ሁልጊዜ ይጻፋል
መልመጃ
አንድ ቁጥር ጥንድ ወይም ጎዶሎ መሆኑን የሚናገር ፕሮግራም ይጻፉ።
መልሱን አሳይ
7 ጎዶሎ ነው