ስተቶችን ማንበብ
ስተት ሲፈጠር ምን ማለት እንደሆነ
ስተት መሥራት የመማር አካል ነው። ጥሩው ዜና አሃዱ ምን እንደተፈጠረ በግልጽ መናገሩ ነው።
እያንዳንዱ ስተት ሦስት ነገር ይዟል፦ ኮድ፣ መልእክት፣ እና ቦታ።
[AH3001] "ያልተሰየመ" የሚባል ተለዋጭ አልተገለጸም።: መስመር 1 ላይ: 4ኛው ካራክተር
AH3001 ኮዱ ነው። መልእክቱ ችግሩን ይናገራል። መስመሩና ዓምዱ የት እንደሆነ ይጠቁማሉ።
ሦስት ዓይነት ስተት
ኮዱ በሚጀምርበት ቁጥር ስተቱ መቼ እንደተገኘ ይታወቃል።
AH1 — የቃላት ስተት
ፕሮግራሙ ወደ ቃላት ሲከፋፈል የሚገኝ። ያልታወቀ ምልክት ሲገባ፦
[AH1001] የማይታወቅ ካራክተር አለ።: መስመር 1 ላይ: 7ኛው ካራክተር
ወይም ክፍተቱ ሲሳሳት፦
[AH1002] የመስመር መጀመሪያ ክፍተት ስተት፡: መስመር 2 ላይ: 1ኛው ካራክተር
AH2 — የአገባብ ስተት
ቃላቱ ትክክል ሆነው አደራደራቸው ሲሳሳት፦
[AH2002] የመዝጊያ ቅንፍ ")" ረስተዋል። የመክፈቻው በመስመር 1 ላይ ነው።: መስመር 1 ላይ: 11ኛው ካራክተር
እነዚህ ሁለቱ ፕሮግራሙ ከመጀመሩ በፊት ይገኛሉ። ስለዚህ አንድም መስመር ሳይሄድ ይነገርዎታል።
AH3 — የአሂድ ስተት
ፕሮግራሙ እየሄደ ሳለ የሚከሰት። እስከዚያ ድረስ ያለው ሁሉ ይሄዳል።
[AH3003] በዘሮ ማካፈል አይቻልም።: መስመር 2 ላይ: 4ኛው ካራክተር
በዜሮ ማካፈል በመጻፍ ጊዜ አይታወቅም — አካፋዩ ዜሮ መሆኑ የሚታወቀው ሲሄድ ነው። ለዚህ ነው AH3 የሆነው።
የተለመዱ ስተቶች
| ኮድ | ትርጉም |
|---|---|
AH3001 |
ያልተሰየመ ተለዋጭ ተጠርቷል |
AH3003 |
በዜሮ ተካፍሏል |
AH3008 |
ከስብስቡ ውጭ ያለ ቦታ ተጠይቋል |
AH1002 |
የመስመር መጀመሪያ ክፍተት ተሳስቷል |
AH2002 |
ቅንፍ አልተዘጋም |
ሙሉው ዝርዝር በማጣቀሻው ውስጥ አለ።
ስተትን እንዴት ማስተካከል
- ኮዱን ያንብቡ — AH1 ወይስ AH3 መሆኑ የት እንደሚፈልጉ ይነግርዎታል
- ወደ መስመሩ ይሂዱ — ስተቱ የተጠቆመው ቦታ ላይ ይጀምሩ
- አንድ ነገር ብቻ ይቀይሩ — ከዚያ እንደገና ያሂዱ
ከላይ ያሉትን ምሳሌዎች ያስተካክሏቸው። ለምሳሌ የመጀመሪያውን ያልተሰየመ
ከመጥራት በፊት ዋጋ ይስጡት።
መልመጃ
ይህ ፕሮግራም ሦስት ስተት አለው። ያግኙና ያስተካክሉ።
[AH1002] የመስመር መጀመሪያ ክፍተት ስተት፡: መስመር 4 ላይ: 1ኛው ካራክተር
መልሱን አሳይ
ስተቶቹ፦ አላስፈላጊ ክፍተት፣ የጎደለ ፦፣ እና ቆጣሪው አለመጨመሩ።
6